ሀዋሳ ከተማ የአሰልጣኙን ውል አራዝሟል

አሠልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት በኃይቆቹ ቤት ለመቆየት በይፋ ውላቸውን አድሰዋል።
\"\"
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከ1990 ጀምሮ ተሳትፎን እያደረጉ ካሉ ሁለት ክለቦች መካከል አንዱ ሀዋሳ ከተማ ነው። ከ2014 ጀምሮ በአሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ እየተመራ ያለፉትን ሁለት የውድድር ዘመናትን ያሳለፈው ክለቡ የአሰልጣኙን ውል ለቀጣዮቹ ዓመታት ለማራዘም የቦርድ አካላት ውይይት ካደረጉ በኋላ ውሳኔ መወሰናቸውን ክለቡ ለሶከር ኢትዮጵያ በላከው መረጃ አመላክቷል።
\"\"
ሲዳማ ቡናን በረዳት እና በዋና አሰልጣኝነት በመምራት የስልጠናውን ዓለም መቀላቀል የቻሉት አሰልጣኙ በመቀጠል በአዳማ ከተማ ከ2014 ጀምሮ ደግሞ ሀዋሳን እያሰለጠኑ የቆዩ ሲሆን ውላቸውን ለተጨማሪ ዓመት በዛሬው ዕለት ካደሱ በኋላ በቀጣዮቹ ቀናት የነባር እና የአዳዲስ ተጫዋቾችን ዝውውር እንደሚያጠናቅቁም ሰምተናል።

\"\"