ፋሲል ከነማ በይፋ አሠልጣኝ ሾሟል

ከሳምንታት በፊት ሶከር ኢትዮጵያ ባስነበበችው ዘገባ መሠረት ዐፄዎቹ ውበቱ አባተን በይፋ በአሠልጣኝነት ሾመዋል።
\"\"
በተጠናቀቀው የቤትኪንገ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 43 ነጥቦችን በመሰብሰብ 6ኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው ፋሲል ከነማ አዲስ አሠልጣኝ ለመሾም በዝግጅት ላይ እንደሚገኝና የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ውበቱ አባተን በመንበሩ ለመቅጠር መወሰኑን ከሳምንታት በፊት ድረ-ገፃችን መዘገቧ ይታወሳል። በዘገባችንም የሊጉ ውድድር ሲገባደድ ክለቡ ጋዜጣዊ መግለጫ ጠርቶ ሽመቱን ለብዙሃን መገናኛ አባላት ይፋ እንደሚያደርግ ጠቁመን ነበር። በዚህ ሂደትም በዛሬው ዕለት ክለቡ አሠልጣኝ ውበቱ አባተን በ3 ዓመት ውል መሾሙን ይፋ አድርጓል።
\"\"
ቦሌ አካባቢ በሚገኘው ጁፒተር ሆቴል እየተከናወነ የሚገኘው የፊርማ ሥነ-ስርዓት እና ጋዜጣዊ መግለጫ በአሁኑ ሰዓት ያልተገባደደ ሲሆን በሥነ-ስርዓቱ ላይ እየተነሱ ያሉ ዝርዝር ጉዳዮች ከቆይታ በኋላ ይዘን የምንመለስ ይሆናል።