መሳይ ደጉ ከማካቢ ሀይፋ ጋር የመጀመርያ ዋንጫውን አነሳ

ቤተ እስራኤላዊ አሰልጣኝ የሱፐር ካፕ ዋንጫ አነሳ።

ባለፈው የውድድር ዓመት ከማካቢ ሁለተኛ ቡድን ጋር አስደናቂ ዓመት አሳልፎ በውድድር ዓመቱ መጀመርያ ዋናውን ቡድን የተረከበው መሳይ የኢስራኤል ሱፐር ካፕን አንስቷል። የኢስራኤል ፕሪምየር ሊግ እና ስቴት ካፕ አሸናፊዎች የሚያገናኘው ዋንጫ ላይ ቤይተር ጄሩሳሌምን ሦስት ለአንድ በማሸነፍ አዲሱን ሹመት በዋንጫ ጀምሮታል።
\"\"
ይህንን ዋንጫም የአሰልጣኝነት ሂወቱ የመጀመርያው ዋንጫ ሲሆን ታላቅ ወንድሙ ብሩክ ደጉ ከዚህ በፊት የእስራኤል ፕሪምየር ሊግ እና ስቴት ካፕ ዋንጫዎች ማንሳቱ ይታወሳል። በ2003 ያሳካው የኢስራኤል የዓመቱ ኮከብ ተጫዋችም በግሉ ያሳካው ትልቁ ስኬት ነው።
\"\"
በቻምፕዮንስ ሊግ ቅድመ ማጣርያ ሀምሩን የተባለ ክለብ ስድስት ለአንድ በሆነ ድምር ውጤት አሸንፈው ወደ ቀጣይ ዙር ያለፉት በመሳይ ደጉ የሚመሩት ማካቢዎች ወደ ቻምፕዮንስ ሊግ ለመግባት በቀጣይ ከሸሪፍ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።