የፈረሠኞቹ እና የጣና ሞገዶቹ ተጋጣሚዎች ቀጣይ ሳምንት ይታወቃሉ

የቻምፒዮንስ ሊግ እና የኮንፌዴሬሽን ካፕ የዕጣ ማውጣት ስነ-ስርዓት በመጪው ማክሰኞ እንደሚካሄድ ታውቋል።

የ2015 የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ አሸናፊዎቹ ቅዱስ ጊዮርጊሶች እና ሊጉን በሁለተኛነት ያጠናቀቁት ባህርዳር ከተማዎች ቀጣይ ዓመት በካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ እና ኮንፌደሬሽን ካፕ ተሳታፊ እንደሚሆኑ ይታወቃል። ሁለት ኢትዮጵያን ወክለው በውድድሩ ተሳታፊ የሚሆኑ ክለቦች በቀጣይ ማክሰኞ በግብፅ ካይሮ በሚካሄደው የዕጣ ማውጣት ስነ-ስርዓት ተጋጣሚዎቻቸውን ያውቃሉ።
\"\"
አምሳ አራት ክለቦች በቻምፕዮንስ ሊግ አምሳ ሁለት ክለቦች ደግሞ በኮንፌደሬሽን ካፕ ተሳታፊ የሚሆኑበት የዘንድሮ ውድድር የአህጉሪቱ ትልቁ ውድድር በታሪክ ለስልሣኛ ዓመት፤ ካፍ ኮንፌደሬሽን ካፕ ደግሞ ለሃያ አንደኛ ዓመት የሚካሄድ ይሆናል።
\"\"
እስካሁን ይፋ የሆነ ዜና ባይኖርም የካፍ አዲሱ ውድድር ማለትም የአፍሪካ እግር ኳስ ሊግ በጥቅምት 2023 ይጀመራል ተብሎ ስለሚጠበቅ የሁለቱ ውድድሮች የመጀመርያ የማጣርያ ጨዋታዎች ከተለመደው ጊዜ ቀደም ብለው ሊካሄዱ እንደሚችሉ ይጠበቃል።