ሲዳማ ቡና ሦስተኛ ተጫዋቹን አስፈርሟል

በሊጉ ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ ለመገኘት የአዳዲስ ተጫዋቾችን ዝውውር እየፈፀመ የሚገኘው ሲዳማ ቡና የአማካይ ስፍራ ተጫዋች የግሉ አድርጓል።
\"\"
በ2016 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ ካለፉት ዓመታት ድክመቱ ተጠናክሮ ለመቅረብ እየጣረ ባለው ክፍት ቦታ የአዳዲስ ተጫዋቾችን ዝውውር እያገባደደ የሚገኘው ሲዳማ ቡና ከደስታ ዮሐንስ እና ብርሀኑ በቀለ በመቀጠል ሦስተኛ ፈራሚው ፍቅረየሱስ ተክለብርሃን መሆኑን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።
\"\"
የቀድሞው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣ ሀዋሳ ከተማ እና ኢትዮጵያ ቡና የመሐል ሜዳ አማካይ ያለፉትን ሁለት የውድድር ዘመናት በሀድያ ሆሳዕና ቆይታውን ካደረገ በኋላ በሁለት ዓመት ውል መዳረሻውን የአሰልጣኝ ሥዩም ከበደውን ሲዳማ ቡና አድርጓል።