ንግድ ባንክ የአንድ ተጫዋች ውል አድሷል

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ከከፍተኛ ሊጉ ካሳደጉ ተጫዋች መካከል አንዱ የሆነው የአማካይ እና የመስመር አጥቂ ስፍራ ተጫዋቹ ውሉን አራዝሟል።
\"\"
የዝውውር መስኮቱን መከፈት ተከትሎ የአዳዲስ ተጫዋቾች እና የነባሮችን ውል በማራዘም የተጠመደው የሊጉ አዲሱ አዳጊ ክለብ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከታችኛው የሊግ ዕርከን ቡድኑን ከፍ ካደረጉ ተጫዋቾች መካከል አንዱ የሆነውን የአማካይ እና የመስመር አጥቂውን ልዑልሰገድ አስፋውን ውል ለተጨማሪ አንድ ዓመት በክለቡ ተራዝሟል።
\"\"
የቀድሞው የአክሱም ከተማ እና ደሴ ከተማ ተጫዋች ሀምበሪቾ ዱራሜን ከለቀቀ በኋላ የተጠናቀቀውን የውድድር ዓመት በንግድ ባንክ ቆይታ የነበረው ሲሆን በፕሪምየር ሊጉም ከክለቡ ጋር ለመቀጠል ውሉን ለተጨማሪ ዓመት ዛሬ አራዝሟል።