ሀዋሳ ከተማ የአጥቂውን ውል አራዝሟል

ኃይቆቹ ከወጣት ቡድኑ የተገኘውን የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች ለሁለት ዓመት ውሉን አራዝመዋል።
\"\"
የአሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉን ውል ካራዘሙ በኋላ ለ2016 የውድድር ዘመን ውላቸው የተጠናቀቁ ተጫዋቾች ውል ማራዘምን ቀዳሚ ተግባራቸው ካደረጉ በኋላ በዛሬው ዕለት ደግሞ እንየው ካሳሁንን የመጀመሪያ ፈራሚያቸው ያደረጉት ሀዋሳ ከተማዎች የወጣቱን አጥቂ ተባረክ ሄፋሞን ውል ለተጨማሪ ዓመት አድሰዋል።
\"\"
በሀዋሳ ከ17 እና ከ20 ዓመት በታች ቡድኖች ውስጥ ሲጫወት ከቆየ በኋላ ወደ ዋናው ቡድን አድጎ ያለፈትን አራት ዓመታት በፕሪምየር ሊጉ ክለቡን እያገለገለ የቆየው አጥቂው ለሁለት ተጨማሪ ዓመት በልጅነት ክለቡ ለማሳለፍ ውሉን አራዝሟል።