ባህርዳር ከተማ አይቮሪኮስታዊ ተከላካይ አስፈርሟል

የጣና ሞገዶቹ የ29 ዓመቱን አይቮሪኮስታዊ ተከላካይ አስፈርመዋል።
\"\"
በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ እና በፕሪምየር ሊጉም ላይ የሚሳተፉት ባህርዳር ከተማዎች በዝውውር ገበያው በንቃት እየተሳተፉ የሚገኝ ሲሆን አሁን ደግሞ ከሀገር ውጪ ፊታቸውን አዙረው አይቮሪኮስታዊውን የ29 ዓመት የመሐል ተከላካይ የሆነውን አብዱላዚዝ ሲአሆን በይፋ አስፈርመዋል።
\"\"
ለሀገሩ ክለቦች ኤ ኤስ ታንዳ ፣ ኤ ኤስ አይ አቤንጎሮው ፣ ከተጫወተ በኋላ በመሐል ወደ ጋቦን አምርቶ ለማይጋ ስፖርት በድጋሜ ወደ ሀገሩ ተመልሶ ያለፉትን ሦስት ዓመታት በለሳት እና ኤል ዋይ ኤስ ሳሳንድራ ከተጫወተ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ባህርዳርን ተቀላቅሏል።