ቡናማዎቹ ከአማካያቸው ጋር በስምምነት ተለያይተዋል

አሠልጣኝ ኒኮላ ካቫዞቪችን ወደ ቡድኑ ያመጣው ኢትዮጵያ ቡና ከአንድ ተጫዋቹ ጋር በስምምነት ተለያይቷል።
\"\"
በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት 43 ነጥቦችን በመሰብሰብ 4ኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው ኢትዮጵያ ቡና በቀጣዩ የውድድር ዓመት ቡድኑን አጠናክሮ ለማቅረብ ከተጫዋቾች ጋር ድርድር እያደረገ ቢገኝም እስካሁን በይፋ ተጫዋች ማስፈረም አልቻለም። ክለቡ በዝውውሩ አዲስ ተጫዋች ባያመጣም ከነባር ተጫዋቾች መካከል ከአማካዩ ሔኖክ ድልቢ ጋር ያለውን ውል በስምምነት ማቋረጡ ታውቋል።
\"\"
በሀዋሳ ከተማ የዕድሜ ዕርከን ቡድኖች ውስጥ በማለፍ ለዋናው ቡድን ከ2009 ጀምሮ መጫወት ችሎ የነበረው ሔኖክ ከ12 ወራት በፊት ኢትዮጵያ ቡናን በሁለት ዓመት ውል ተቀላቅሎ የነበረ ቢሆንም ቀሪ የአንድ ዓመት ውል እያለው በዛሬው ዕለት ከክለቡ ጋር በስምምነት መለያየቱ ታውቋል።