ቅዱስ ጊዮርጊሶች የአምስት ተጫዋቾችን ውል አድሰዋል

ከሰዓታት በፊት የአማኑኤል አረቦን ዝውውር የፈፀሙት ቅዱስ ጊዮርጊሶች የአምስት ወጣት ተጫዋቾችን ውል ማደሳቸውን ይፋ አድርገዋል።
\"\"
ከሰሞኑን የነባር ተጫዋቾችን ውል የማደስ ሥራ ላይ የነበሩት ቅዱስ ጊዮርጊሶች በዛሬው ዕለት በይፋ ወደ ዝውውሩ የገቡ ሲሆን አማኑኤል አረቦን የመጀመሪያ ፈራሚያቸው አድርገው እንዳስፈረሙ ለሰዓታት በፊት ዘግበን ነበር። ክለቡ ከግብ ጠባቂ ጀምሮ ሌሎች ተጫዋቾችን ለማስፈረም ድርድር ላይ እንዳለ የተሰማ ሲሆን ጎን ለጎን የነባር ተጫዋቾችንም ውል አድሷል።
\"\"
በዚህም ከተስፋ ቡድን ጀምሮ ቡድኑን እያገለገሉ የሚገኙት ዳግማዊ አርአያ፣ አብርሃም ጌታቸው፣ ተገኑ ተሾመ፣ አላዛር ሳሙኤል እና ሻይዱ ሙስጠፋ ለሁለት ተጨማሪ ዓመት በክለቡ ለመቆየት ውላቸውን አድሰዋል።