ፈረሰኞቹ አጥቂ አስፈርመዋል

ቅዱስ ጊዮርጊሶች የአጥቂ መስመር ተጫዋች አስፈርመዋል።
\"\"
የ2015 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫ ባለቤቶቹ ቅዲስ ጊዮርጊሶች ከሰሞኑን የነባር ተጫዋቾችን ውል ማደስ ላይ ተጠምደው የነበረ ሲሆን ዛሬ በይፋ አዳዲስ ተጫዋቾችን ማስፈረም ጀምረዋል። በዚህም ከደቂቃዎች በፊትም በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በለገጣፎ ለገዳዲ ያሳለፈውን አማኑኤል አረቦ የመጀመሪያ ፈራሚያቸው ማድረጋቸውን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።
\"\"
በአርባምንጭ ከተማ ደደቢት ከሚባል ፕሮጀክት የተገኘው አማኑኤል በጎፋ ባረንቼ እና በለገጣፎ ለገዳዲ ካሳለፈ በኋላ መዳረሻው ቅዱስ ጊዮርጊስ ሆኗል።