ቅዱስ ጊዮርጊስ ግብ ጠባቂ አስፈርሟል

ፈረሰኞቹ ሁለተኛ ተጫዋቻቸውን በይፋ በዛሬው ዕለት አስፈርመዋል።
\"\"
ለካፍ ቻምፒየንስ ሊግ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ የቅደመ ውድድር ዝግጅቱን በዛሬው ዕለት በቢሾፍቱ ከተማ የሚጀምሩት ቅዱስ ጊዮርጊሶች ከቀናት በፊት አማኑኤል አረቦን የመጀመሪያ ፈራሚ ያደረጉ ሲሆን በዛሬው ዕለት ደግሞ ሁለተኛ ፈራሚያቸው ግብ ጠባቂው ፋሲል ገብረሚካኤል በሁለት ዓመት ውል ሆኗል።
\"\"
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ውስጥ በቋሚ ግብ ጠባቂነት በርካታ ጨዋታዎችን ያደረገው እና በሰበታ ከተማ እና ያለፉትን ሁለት ዓመታት ደግሞ በባህርዳር ከተማ ቆይታ የነበረው ግብ ጠባቂው ለቀጣይ የእግር ኳስ ህይወቱ ፈረሰኞቹን መርጦ ተቀላቅሏል።