የላሜስያ አካዳሚ ውጤት የሆነው ተጫዋች ወደ አዲስ ክለብ አምርቷል

አስቻለው ሳንማርቲ አዲስ ክለብ ተቀላቀለ።

የባርሰሎና አካዳሚ ውጤት የሆነው አስቻለው ሳንማርቲ አዲስ ክለብ ተቀላቀለ። ባለፈው የውድድር ዓመት በታችኛው ሊግ በሚሳተፈው ኮርኔላ ቆይታ የነበረው ተጫዋች የካታላኑ ክለብ ለቆ በቫለንሲያ ግዛት የሚገኘው ኦሪህዌላ የተባለ ክለብ ተቀላቅሏል።
\"\"
ለአራት ዓመታት ማለትም እስከ 2019 ድረስ ከስፔኑ ታላቅ ክለብ ጋር ቆይታ የነበረው እና ባለፈው የውድድር ዓመት በሦስተኛው የሊግ እርከን በሚሳተፈው ኮርኔላ ያሳለፈው ይህ አማካይ ከክለቡ ጋር የነበረው ውል መጠናቀቁን ተከትሎ በአንድ ዓመት ውል ኦርህዌላን ተቀላቅሏል።
\"\"
ሌላው ከአስቻለው በተመሳሳይ የባርሰሎና ወጣት ቡድን አባል የነበረው እና በ2020 የካታለሎኑን ክለብ ለቆ ወደ ጣልያን በማምራት ከዚህ ቀደም እዮብ ዛምባታሮ በተጫወተበት አታላንታ እና ሄላስ ቬራና ቆይታ የነበረው እንዲሁም ትልቅ ተስፋ ተጥሎበት የነበረው አንዋር ማዴይሮ በአሁኑ ሰዓት በዩናይትድ ዓረብ ኤሜሬትስ ሁለተኛ የሊግ እርከን ተሳታፊ በሆነውን ፉርሳን ሂስፓኒና የተሰኘ ክለብ እየተጫወተ ይገኛል።