አዳማ ከተማ ሦስት ተጫዋቾችን አስፈረመ

የአሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለ አዳማ ከተማ በዛሬው ዕለት ወደ ዝውውር በመግባት የሦስት ተጫዋቾችን ዝውውር አጠናቋል።

በ2015 የውድድር ዘመን በአሰልጣኝ ይታገሱ እንዳለ እየተመራ በርካታ ወጣት ተጫዋቾችን በሊጉ ያስመለከተን እና በክረምቱ በርከት ያሉ ነባር ተጫዋቾቹን ያጣው አዳማ ከተማ በዛሬው ዕለት ወደ ዝውውሩ ጎራ በማለት ሦስት አዳዲስ ተጫዋቾችን የግሉ ማድረጉን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።
\"\"
የክለቡ የመጀመሪያው ፈራሚ ሱራፌል ዐወል ሆኗል። በአማካይ ቦታ እና በመስመር አጥቂነትም ጭምር በጅማ አባቡና እና ጅማ አባጅፋር ሲጫወት የሚታወቀው እና በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት አጋማሽ ደግሞ በለገጣፎ ለገዳዲ ቆይታ የነበረው ተጫዋቹ ቀጣዩ መዳረሻው አዳማ ከተማ ሆኗል።

ሁለተኛው የክለቡ አዲሱ ተጫዋች አሸናፊ ኤልያስ ነው። ከአርባምንጭ ከተማ ወጣት ቡድን ከተገኘ በኋላ ዋናውን ቡድን ያለፉትን አራት ዓመታት ያገለገለው ተጫዋቹ ቀጣይ መዳረጋቸው አዳማ ከተማ መሆኑ ዕርግጥ ሆኗል።
\"\"
ሌላኛው ፈራሚ ፍቅሩ አለማየሁ ነው። በግራ መስመር ተከላካይነት በለገጣፎ ለገዳዲ በፕሪምየር ሊጉ ያሳለፈው ተጫዋቹ ሦስተኛው የአዳማ ከተማ ፈራሚ ነው።