የጣና ሞገዶቹ የወሳኝ ተጫዋቻቸውን ውል አድሰዋል

በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ የሚጠብቀው ባህርዳር ከተማ የአማካዩን ውል ለተጨማሪ ዓመታት አራዝሟል።

\"\"
በ 2015 ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ደረጃን ይዘው በማጠናቀቅ ለመጀመሪያ ጊዜ በአህጉራዊ ውድድሮች ላይ የመሳተፍ ዕድል ያገኙት ባህር ከተማዎች ከሰሞኑ የበርካታ ክለቦችን ትኩረት ስቦ የነበረውን ወሳኝ አማካያቸውን አለልኝ አዘነ ውል ማደሳቸውን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።

\"\"
ከአርባምንጭ ከተማ ተስፋ ቡድን የተገኝቶ እስከ ዋናው ቡድን ድረስ መጫወት የቻለው አለልኝ በሀዋሳ ከተማ እንዲሁም ያለፉትን ሁለት ዓመታት በጣና ሞገዶቹ ቤት ቆይታ ማድረጉ ይታወሳል። ሆኖም ተጫዋቹ በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታትም በጣና ሞገዶቹ ቤት ለመቆየት ዛሬ ውሉን አራዝሟል።