ወላይታ ድቻ የግራ መስመር ተከላካይ አስፈረመ

የአሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ ወላይታ ድቻ አምስተኛ ተጫዋች የግሉ አድርጓል።
\"\"
ለፕሪምየር ሊጉ የቀጣይ ዓመት ጉዟቸው ቡድናቸውን እያጠናከሩ የሚገኙት የጦና ንቦቹ በአሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ መሪነት ባዬ ገዛኸኝ ፣ አብነት ደምሴ ፣ ፀጋዬ ብርሃኑ እና ብዙአየው ሰይፈን የግላቸው ከማድረጋቸው በተጨማሪ የወሳኝ ተጫዋቾቻቸውን ውልም ለተጨማሪ ዓመታት ከቀናት በፊት ማራዘማቸው ይታወሳል። አሁኑ ደግሞ ቡድኑ አምስተኛ አዲስ ፈራሚ በማድረግ የግራ መስመር ተከላካይ የሆነውን ፍፀም ግርማን ወደ ስብሰባቸው መቀላቀላቸውን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።
\"\"
በአንደኛ ሊጉ ወሊሶ ከተማ በመጫወት የእግር ኳስ ህይወቱን የጀመረው ተጫዋቹ በመቀጠል ወደ ትውልድ ሀገሩ ወልቁጤ ከተማ ከዛም ወደ ኢኮስኮ አምርቶ መጫወት የቻለ ሲሆን ያለፉትን ሁለት የውድድር ዘመናት ወደ ቀድሞው ክለቡ ወልቂጤ ተመልሶ በመጫወት ቆይታይ ካደገ በኋላ በእግር ኳስ ህይወቱ አራተኛ ክለቡ ወላይታ ድቻ ሆኗል።