ፈረሰኞቹ ናይጄሪያዊ አጥቂ ለማስፈረም ተስማምተዋል

የወቅቱ የሊጉ ሻምፒዮን ቅዱስ ጊዮርጊስ የአጥቂ መስመር ተጫዋች ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል።
\"\"
ያለፉትን ሁለት ዓመታት የሊጉን ዋንጫ ያነሳው ቅዱስ ጊዮርጊስ በካፍ ቻምፒየንስ ሊግ ላለበት የማጣሪያ ጨዋታ እና ለ2016 የሊጉ ውድድር በትናንትናው ዕለት ዝግጅቱን ደብረ ዘይት ላይ ጀምሯል። በዝውውሩ የነባር ተጫዋቾችን ውል ከማደስ ጎን ለጎን አማኑኤል አረቦ፣ ፋሲል ገብረሚካኤል እና ክዋሜ አዶም ፍሪምፓንግን ያስፈረሙ ሲሆን አሁን ደግሞ ናይጄሪያዊ አጥቂ ለማስፈረም ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።

ፈረሰኞቹን ለመቀላቀል ቅድመ ስምምነት የፈፀመው ተጫዋች ሞሰስ ኦዶ ቶቹኩ ነው። አንድ ሜትር ከሰማንያ ሦስት ሴንቲ ሜትር የሚረዝመው ተጫዋቹ በሀገሩ ናይጄሪያ፣ ግብፅ፣ ኢራን፣ ሳይፕረስ፣ ሱዳን እና ቻይና ሊግ ረዘም ያለ የእግርኳስ ህይወት አሳልፏል።
\"\"
ሁለቱ የውጪ ሀገር ተጫዋቾች ሞሰስ ቶቹኩ እና ክዋሜ ፍሪምፖንግ ዛሬ ወይም ነገ ወደ አዲስ አበባ እንደሚገቡና በይፋ ክለቡን እንደሚቀላቀሉ ሰምተናል።