ኢትዮጵያ ቡና የመጀመሪያ ፈራሚው ታውቋል

በከፍተኛ ሊጉ በሀምበሪቾ ዱራሜ ጥሩ የውድድር ዓመት ያሳለፈው ግብ ጠባቂ ወደ ኢትዮጵያ ቡና አምርቷል።
\"\"
ከቀጣዩ የውድድር ዘመን አንስቶ በሰርቪያዊው አሰልጣኝ ኒኮላ ካቫዞቪችን እንደሚመራ የሚጠበቀው ኢትዮጵያ ቡና በርካታ ተጫዋቾች በክለቡ ውል ያላቸው በመሆኑ በዚህ ክረምት የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ጥቂት ተሳትፎን ብቻ እንደሚያደርግ ተሰምቷል። ክለቡም ወደ ዝውውሩ በዛሬው ዕለት በመግባት በሁለት ዓመት ውል የመጀመሪያ ፈራሚው ግብ ጠባቂው አስራት ሚሻሞ ሆኗል።
\"\"
የቀድሞው የወላይታ ድቻ ፣ ሀድያ ሆሳዕና ፣ ሺንሺቾ ከተማ እና ሀምበሪቾ ዱራሜ ግብ ጠባቂ የነበረው አስራት የተጠናቀቀውን የውድድር ዘመን ሀምበሪቾ ዱራሜ ወደ ፕሪምየር ሊጉ እንዲያድግ ቁልፍ አስተዋጽኦን ያደረገ ሲሆን ቀጣዩ መዳረጋቸው ኢትዮጵያ ቡና ሆኗል።