ንግድ ባንክ ጋናዊ ተጫዋች ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከላካይ እና አማካይ ቦታ ላይ መጫወት የሚችል ጋናዊ ተጫዋች አስፈርሟል።
\"\"
በ2016 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ ለመገኘት የአዳዲስ ተጫዋቾችን ዝውውር እየፈፀመ የሚገኘው እና ጎን ለጎንም በክለቡ ያሉ ነባሮችንም ውል እያደሰ የሚገኘው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋናዊውን የ25 ዓመት ካሌብ አማንኩዋን በአንድ ዓመት ውል የስብስቡ አካል አድርጓል።
\"\"
1 ሜትር ከ85 ሴንቲ ሜትር የሚረዝመውና በሀገሩ ጋና ክለቦች ዋፋ ፣ አዱዋና ስታርስ እና ህርትስ ኦፎክ መጫወት የቻለው ይህ ተጫዋች በተከላካይነት እና በአማካይ ተከላካይነት ቦታ ላይ መጫወት የሚችል ሲሆን ቀጣዩም መዳረሻው አዲስ አዳጊው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሆኗል።