ሃሩን ኢብራሂም በቻምፒየንስ ሊግ ማጣርያ በሚሳተፈው ቡድን ተካተተ

የኖርዌዩ ታላቅ ክለብ ሞልደ ዛሬ ማታ ለሚያደርገው ወሳኝ የቻምፒየንስ ሊግ ጨዋታ ትውልደ ኢትዮጵያዊው ተጫዋች በቡድኑ ውስጥ አካተተ።
\"\"
ከኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች የተገኘው የሀያ ዓመቱ ሃሩን ኢብራሂም በቻምፒየንስ ሊግ ቅድመ ማጣርያ ይሳተፋል። በኖርዌዩ ታላቅ ክለብ ሞልደ በመጫወት ላይ የሚገኘው ይህ ወጣት ተጫዋች ክለቡ ሞልደ ዛሬ ማታ ከሄልሲንኪ ጋር ለሚያደርገው የቻምፕዮንስ ሊግ ቅድመ ማጣርያ ሁለተኛ ጨዋታ በቡድኑ ውስጥ መካተት ችሏል።
\"\"
ባለፈው የውድድር ዓመት በ0.2 ሚልዮን ዩሮ የስዊድኑን ክለብ GAIS Göteborg ለቆ የኖርዌዩን ክለብ የተቀላቀለው ይህ ተጫዋች ቡድኑ ሞልድ አንድ ለባዶ በተሸነፈበት የመጀመርያው ጨዋታ ያልተሳተፈ ሲሆን ዛሬ ግን በወሳኙ ጨዋታ ቡድኑን ለማገልገል በተቀያሪ ወንበር ላይ ሆኖ ጨዋታውን ጀምሯል።