የ2015 የሊጉ ኮከቦች ሽልማት የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆኗል

ከወትሮ በተለየ ሁኔታ የዓመቱ ኮከቦችን ሽልማት መዘግየትን በተመለከተ በትናንትናው ዕለት በሶከር ኢትዮጵያ ገለፃ ያደረገው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አክሲዮን ማኅበር ሽልማቱ የሚሰጥበትን ቀን ይፋ አድርጓል።

ከደቂቃዎች በፊት የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መርሐ-ግብር ይፋ መሆኑ ይታወቃል። በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ኮከብ ሆነው ያጠናቀቁ ግለሰቦችን ሽልማት በተመለከተ የአክሲዮን ማኅበሩ ሥራ-አስኪያጅ አቶ ክፍሌ ሰይፈ በትናንትናው ዕለት ገለፃ አድርገው የነበረ ሲሆን በእጣ መውጣት መርሐ-ግብሩ ላይ ሽልማቱ የሚሰጥበትን ቀን ይፋ አድርገዋል።

“የስያሜ መብቱ መጓተት የሽልማት መርሐ-ግብሩን አዘግይቶታል። ይህ ልክ አይደለም። የሽልማቱንም ለዛ አደብዝዞታል። ግን ነሐሴ 13 በሀያት ሪጀንሲ ሆቴል የ2015 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የኮከቦች ሽልማት ይከናወናል። ከዚሁ ዕለት ሦስት ታላላቅ ስምምነቶችን ይፋ እናደርጋለን።” በማለት ተናግረዋል።