ብርቱካናማዎቹ የአማካያቸውን ውል አራዝመዋል

ድሬዳዋ ከተማ የአማካያቸውን ኮንትራት ለተጨማሪ ዓመት አራዝመዋል።

በአሰልጣኝ አስራት አባተ መሪነት እስከ አሁን የአምስት ተጫዋቾችን ዝውውር የቋጩት ድሬዳዋ ከተማዎች ከአዳዲስ ፈራሚዎች ጎን ለጎን በክለቡ ውላቸው የተጠናቀቁ ተጫዋቾችን ውል ለተጨማሪ ዓመታት ሲያራዝሙ የነበረ ሲሆን በዛሬው ዕለት ደግሞ በአምበልነት እና በአማካይነት ቡድኑን በሁለተኛው ዙር ተቀላቅሎ ያገለገለውን ዳዊት እስጢፋኖስን ኮንትራት ለተጨማሪ ዓመት ማራዘማቸውን ዝግጅት ክፍላችን አውቃለች።

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፣ መከላከያ ፣ ደደቢት ፣ ኢትዮዽያ ቡና ፣ ኢትዮ ኤሌትሪክ ፣ ፋሲል ከተማ ፣ ሰበታ እና ጅማ አባጅፋር ተጫውቶ ያሳለፈው አማካዩ ወደ ቀድሞው ክለቡ ድሬዳዋ ተመልሶ በዓመቱ አጋማሽ የተቀላቀለ ሲሆን ለተጨማሪ አንድ ዓመት የሚያቆየውን ውልም በዛሬው ዕለት ተጫዋቹ በክለቡ አራዝሟል።