መድን አጥቂ አስፈርሟል

የአሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌውን ኢትዮጵያ መድን የአጥቂ ስፍራ ተጫዋች አስፈርሟል።

በ2016 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ ከተጠናቀቀው ዓመት በተሻለ ሆኖ ለመገኘት አዳዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም እና የነባሮችንም ውል ሲያድስ የነበረው ኢትዮጵያ መድን ከነገ ጀምሮ በአዳማ ከተማ የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን እንደሚጀምር የሚጠበቅ ሲሆን በዛሬው ዕለትም የአጥቂ ስፍራ ተጫዋቹ መሐመድ አበራን በሁለት ዓመት ውል አስፈርሟል።

ከመቻል ወጣት ቡድን ከተገኘ በኋላ በዋናው ቡድን እንዲሁም በሰበታ ከተማ ተጫውቶ የተጠናቀቀውን ዓመት ደግሞ በለገጣፎ ለገዳዲ ያሳለፈው ተጫዋቹ በዛሬው ዕለት አዲሱ የመድን ፈራሚ መሆኑን አረጋግጠናል።