ወላይታ ድቻ የመስመር ተከላካዩን ውል አድሷል

የአሰልጣኝ ያሬድ ገመቹው ወላይታ ድቻ የመስመር ተከላካዩን ኮንትራት ለተጨማሪ ዓመት አራዝሟል።

በ2016 የውድድር ዘመን በአሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ መሪነት ወደ ሊጉ የሚመመለሱት ወላይታ ድቻዎች የሚያስፈልጓቸውን አዳዲስ ተጫዋቾች ከማስፈረም በዘለለ ውላቸው የተጠናቀቁትም እያስፈረሙ የቆዩ ሲሆን የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውንም በነገው ዕለት ይጀምራሉ። ክለቡ ዝግጅት ከመጀመሩ አስቀድሞ ውሉ ተጠናቆ የነበረው የመስመር ተከላካዩ አናጋው ባደግን ኮንትራት አድሷል።

ከዚህ ቀደም በወላይታ ድቻ ከተጫወተ በኋላ በድሬዳዋ ፣ ደቡብ ፓሊስ እና መቻል ቆይታን በማድረግ ዳግም ወደ ቀድሞው ክለቡ ድቻ ተመልሶ ቆይታን ያደረገው ተጫዋቹ በክለቡ ውሉ መጠናቀቁን ተከትሎ ኮንትራቱን አራዝሟል።