ፋሲል ከነማ የመስመር ተከላካይ አስፈርሟል

በሀዋሳ የቅድመ ውድድር ዝግጅት እየሰሩ የሚገኙት ዐፄዎቹ የመስመር ተከላካይ በሦስት ዓመት ውል አስፈርመዋል።

በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ መሪነት ማረፊያቸውን በሀዋሳ ታደሰ እንጆሪ ሆቴል በማድረግ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን እየሰሩ የሚገኙት ፋሲል ከነማዎች በክረምቱ የዝውውር መስኮት ቃልኪዳን ዘላለም ፣ ምኞት ደበበ ፣ አማኑኤል ገብረሚካኤል ፣ እዮብ ማቲዮስ ፣ ጌታነህ ከበደ እና ጋቶች ፓኖምን ወደ ስብስባቸው የቀላቀሉ ሲሆን የመስመር ተከላካይ ስፍራ ተጫዋቹን ዮናታን ፍሰሀን በሦስት ዓመት ውል ሰባተኛ ፈራሚያቸው ስለማድረጋቸው ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።

እግር ኳስን በትውልድ ሀገሩ አዳማ ካደረገ በኋላ በተለይ በሲዳማ ቡና ከብዙሀኑ የስፖርት ቤተሰብ ጋር መተዋወቅ የቻለው ተጫዋቹ በመቀጠል ወደ ወልቂጤ በማምራትም መጫወት ችሏል። በገጠመው ጉዳት የተነሳ ከሜዳ ርቆ የሰነበተው ዮናታን ከጉዳቱ ሙሉ በሙሉ በማገገመ ዳግም ወደ ፕሪምየር ሊጉ የተመለሰበትን ዝውውር በዐፄዎቹ ቤት ፈፅሟል።

ክለቡ በቀጣዮቹ ቀናትም ሙከራ እየሰጣቸው ያሉን ጨምሮ የውጪ ዜጋ ተጫዋቾችን እንዲሁም ተጨማሪ የአሰልጣኝ ቡድን አባላትን እንደሚቀጥር ይጠበቃል።