ሀይደር ሸረፋ ማረፊያው ታውቋል

ከአራት ዓመታት በኋላ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የተለያየው አማካዩ ሀይደር ሸረፋ ወደ አዲስ ክለብ አምርቷል።

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የቀጣይ ዓመት ተሳትፎውን ለማድረግ የቅድመ ውድድር ዝግጅቱን በክለቡ መቀመጫ ከተማ እያደረገ የሚገኘው አዳማ ከተማ የክለቡ 12ኛ አዲስ ፈራሚ አድርጎ አማካዩ ሀይደር ሸረፋን ወደ ስብስቡ ስለ መቀላቀላቸው ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ያመለክታል።

በአማካይ ስፍራ ላይ በደደቢት ፣ ሀድያ ሆሳዕና እና ጅማ አባቡና የተጫወተው ሀይደር ከመቐለ 70 እንደርታ ጋር የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ ካሳካ በኋላ ወደ ቅዱስ ጊዮርጊስ አምርቶ ያለፉትን አራት ዓመታት ክለቡን በአምበልነትም ጭምር እየመራ በተከታታይ ሁለት ዓመት የሊጉን ዋንጫ ከክለቡ ጋር አሳክቷል። በያዝነው ክረምት ውሉ ከፈረሰኞቹ ጋር የተጠናቀቀው ተጫዋቹ በእግር ኳስ ህይወቱ ስድተኛ ክለቡ አዳማ ከተማ መሆኑ ዕርግጥ ሆኗል።