አዲስ አዳጊው ሀምበሪቾ ዱራሜ ወደ ዝውውር ገብቷል

በቀጣዩ ዓመት በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ላይ የሚካፈለው ሀምበሪቾ ዱራሜ አራት አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የአስር ነባሮችን ውልም አራዝሟል።

ከከፍተኛ ሊጉ ለመጀመሪያ ጊዜ በማደግ በ2016 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሳተፈው ሀምበሪቾ ዱራሜ በሊጉ ላይ ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ ለመገኘት አስቀድሞ ከታች ያሳደገውን የአሰልጣኝ አስራት ዮሐንስን ኮንትራት ካራዘመ በኋላ በመቀጠል ወደ ዝውውሩ በመግባት አራት አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የአስሩን  ኮንትራት ማደሱን ክለቡ ለዝግጅት ክፍላችን ይፋ አድርጓል።


ብርሀን ገብረስላሴ አማካይ ከአቃቂ ቃሊቲ ፣ ብዙነሸ  እሸቱ ተከላካይ ከቦሌ ክፍለከተማ ፣ ሳሮን ሰመረ አጥቂ ከንፋስ ስልክ እና ወርቅነሸ ዘሪሁን ተከላካይ ከሱሉለታ ከተማ የክለቡ አዳዲስ ፈራሚ ሆነዋል።


ክለቡን ከታችኛው የሊግ ዕርከን ያሳደጉ ኤልሳቤጥ ታምሩ ፣ ፍሬነሽ ዮሐንሰ ፣ ሠላም ፀጋዬ ፣ ብዙአየሁ አበራ ፣ መልካም አለማየሁ ፣ ዝናሸ አበራ ፣ ዘሪቱ ብርሀኑ ፣ ሰናይት ኤልያሰ ፣ ከምባቴ ካቴሊ እና ዝናሸ ሰለሞን በበኩላቸው ውላቸው ታድሶላቸዋል።