ኢትዮጵያ ቡና አማካይ አስፈርሟል

ከኢትዮጵያ ቡና ጋር የሙከራ ጊዜውን ሲያሳልፍ የነበረው የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ ናሆም ጌታቸው በሦስት ዓመት ውል ክለቡን ተቀላቅሏል።

በአዳማ ከተማ መቀመጫቸውን በማድረግ በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ስታዲየም የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን እየከወኑ የሚገኙት ኢትዮጵያ ቡናዎች በቅድመ ውድድር ዝግጅት ወቅት የሙከራ ዕድል ሰጥተውት የነበረውን የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹን ናሆም ጌታቸውን በሦስት ዓመት ውል ወደ ስብስባቸው ተቀላቅለዋል።

ከኢትዮጵያዊ ቤተሰቦች የተገኘው እና የአሜሪካ ዜግነትን በጣምራ እንደያዘ የሚነገርለት ናሆም በዛው በአሜሪካ በዩኒቨርስቲ ኦፍ ሀውስተን እና ኢትዮጵያዊያን በሚሳተፉበት የክረምት ውድድር ላይ በኢትዮ ዳላስ ቡድን ውስጥ የነበረ ሲሆን በኢትዮጵያ ቡና የሙከራ ጊዜውን አጠናቆ በሦስት ዓመት ውል ለክለቡ ፊርማውን አኑሯል።