የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጥሪ ይፋ ሆኗል

ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የመጨረሻ የምድብ ጨዋታ ወደ ግብፅ የሚያቀናው የዋልያዎቹ የመጨረሻ ስብስብ ታውቋል።

በምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ኮትዲቯር የሚከናወነው የ2023ቱ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ወደ መጨረሻው ምዕራፍ ተቃርቧል።

በውድድሩ ማጣሪያ በምድብ አራት ተደልድሎ ጨዋታዎቹን ሲያከናውን የቆየው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ምንም እንኳን መውደቁን ቢያረጋግጥም የመጨረሻ የምድብ ጨዋታውን የፊታችን ጷግሜ 03 ከግብፅ ጋር እንደሚያከናውን ይጠበቃል። ከዚህ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በነገው ዕለት ከ08:00 ጀምሮ ጁፒተር ሆቴል ተገኝተው ሪፖርት እንዲያደርጉ መልዕክት ያስተላለፈላቸውን የመጨረሻ 23 ተጫዋቾች አሳውቋል።

ፌዴሬሽኑ ከደቂቃዎች በፊት ይፋ ያደረገው የ23 ተጫዋቾች ዝርዝር ፦

ግብ ጠባቂዎች

ሰዒድ ሐብታሙ (አዳማ ከተማ)
አቡበከር ኑራ (ኢትዮጵያ መድን)
ቢኒያም ገነቱ (ወላይታ ድቻ)

ተከላካዮች

ምኞት ደበበ (ፋሲል ከነማ)
ሚሊዮን ሰለሞን (ሀዋሳ ከተማ)
አስቻለው ታመነ (መቻል)
አማኑኤል ተረፉ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
ሔኖክ አዱኛ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
ረመዳን የሱፍ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
ዓለምብርሀን ይግዛው (ፋሲል ከነማ)
ፍራኦል መንግሥቱ (ባህር ዳር ከተማ)

አማካዮች

አማኑኤል ዮሐንስ (ኢትዮጵያ ቡና)
ጋቶች ፓኖም (ፋሲል ከነማ)
ከነዓን ማርክነህ (መቻል)
ሽመልስ በቀለ (ኤል ጉና)
ሱራፌል ዳኛቸው (ፋሲል ከነማ)
ፍፁም ጥላሁን (ባህር ዳር ከተማ)
ወገኔ ገዛኸኝ (ኢትዮጵያ መድን)
ቢኒያም በላይ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)

አጥቂዎች

አቤል ያለው (ቅዱስ ጊዮርጊስ)
ሀብታሙ ታደሰ (ባህር ዳር ከተማ)
ዳዋ ሆቴሳ (ሀዲያ ሆሳዕና)
ቸርነት ጉግሳ (ባህር ዳር ከተማ)