ከፍተኛ ሊግ የሚጀምርበት ቀን ይፋ ሆኗል

በሁለት ምድብ ተከፍሎ እንደሚደረግ የሚጠበቀው የ2016 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር የዕጣ ማውጣት መርሀግብር እና የሚጀመርበትን ቀን ፌድሬሽኑ አሳውቋል።

ካለፉትን ዓመታት አንፃር የክለቦችን ቁጥር እና አንድ ምድብን ለውድድሩ ጥራት በሚል በመቀነስ የሚደረገው የ2016 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር በሁለት ምድብ ተከፍሎ በ26 ክለቦች መካከል እንደሚደረግ ይጠበቃል። ከዘንድሮው ዓመት ውድድር ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን የዕጣ ማውጣት እና የውድድሩን መጀመሪያ ቀን ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሠረት የዕጣ ማውጣቱ ሥነ ስርዓት ጥቅምት 3 ከተከናወነ በኋላ ውድድሩ ጥቅምት 17 እንደሚጀመር ነው የታወቀው። ፌድሬሽኑ አያይዞም ክለቦች እስከ መስከረም 11 ምዝገባን የዳኞች እና ታዛቢዎች ክፍያን እስከ መስከረም 30 እንዲያጠናቅቁ አሳስቦ ክፍያ ያላጠናቀቀ ክለብ በዕጣ ማውጣቱ ስነ ስርዓት ላይ የማይሳተፍ መሆኑ ተገልጿል።