ወላይታ ድቻ ሁለት ረዳት አሰልጣኞችን ቀጥሯል

ወላይታ ድቻ የአሰልጣኝ ቡድን አባላቱን አደራጅቶ ጨርሷል።

በአዲሱ አሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ እየተመሩ በክለቡ መቀመጫ ከተማ በሆነችው ሶዶ ላይ የቅድመ ውድድር ዝግጅቶቻቸውን እየሰሩ የሚገኙት ወላይታ ድቻዎች ወደ ሀዋሳ በመምጣት በሲዳማ ጎፈሬ ዋንጫ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ። እስከ አሁን ተጫዋቾችን በማዘዋወር ተጠምዶ የሰነበተው ክለቡ የአሰልጣኝ ቡድኑን ለማጠናከር ሁለት ረዳት አሰልጣኞችን ወደ ስብስቡ ማካተቱም ትልውቋል።

ቅዱስ ዘሪሁን የክለቡ ረዳት አሰልጣኝ ሆኗል። በሀዋሳ የተለያዩ ቡድኖችን ያሰለጠነው እና በመቀጠል በሀዋሳ ከተማ ያለፉትን ሁለት ዓመታት ደግሞ የሀድያ ሆሳዕና የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ የነበረ ሲሆን በሀድያ ሆሳዕና አብሮ ከሰራው አሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ ጋር በቀጣይም ዳግም ለመስራት ረዳት ሆኖ በክለቡ ተቀጥሯል።

ግዛቸው ጌታቸውም በድጋሚ ወደ ቀደመ ክለቡ ተመልሷል። ወላይታ ድቻን በተጫዋችነት በወጣት ቡድን አሰልጣኝነት ያገለገለው እና እንዲሁም በዋናው ቡድን ውስጥም በረዳት አሰልጣኝነት የሰራ ሲሆን ጋሞ ጨንቻንም በከፍተኛ ሊጉ አሰልጥኖ አልፏል። በድጋሚ ወደ ቀድሞ ክለቡ ተመልሶም ረዳት ሆኗል።

ከሁለቱ አዳዲስ ረዳት አሰልጣኞች በተጨማሪ ክለቡ የግብ ጠባቂ አሰልጣኙ ዘላለም ማቲዮስን ውልም አራዝሟል።