አዲስ አበባ ከተማ የበርካታ ተጫዋቾችን ዝውውር ቋጭቷል

በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ላይ የሚካፈለው የመዲናይቱ ክለብ የበርካታ ተጫዋቾችን ዝውውር አጠናቋል።

በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ ላይ የሚሳተፈው የአሰልጣኝ አብዱራህማን ዑስማኑ አዲስ አበባ ከተማ ለ2016 የውድድር ዘመን ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ ለመገኘት አስራ ስድስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርም የሰባት ነባሮችን አራዝሟል።

የክለቡ አዳዲስ ፈራሚዎች የቀድሞዋ የንግድ ባንክ ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ባህር ዳር ተከላካይ አዳነች ጌታቸው ፣ በሲዳማ ፣ መቐለ ፣ ኤሌክትሪክ እና ንግድ ባንክ የተጫወተችው አጥቂዋ ዮርዳኖስ ምዑዝ ፣ አይናለም አለማየሁ አማካይ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ ዳግማዊት ሰለሞን አጥቂ ከይርጋጨፌ ቡና ፣ እየሩስ ወንድሙ አጥቂ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ ትዕግስት ኃይሉ ተከላካይ ከኤሌክትሪክ ፣ የምስራች ሞገስ ተከላካይ ከቦሌ ፣ ቤዛዊት ድምፀ ተከላካይ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ መታሰቢያ ክፍሌ ተከላካይ ከይርጋጨፌ ቡና ፣ ወርቅነሽ መሠለ አማካይ ከአርባምንጭ ፣ ሒሩት ተስፋዬ አማካይ ከቦሌ ፣ ቻይና ግዛቸው አማካይ ከአዳማ ፣ ፍቅርተ ካሳ አማካይ ከባህር ዳር ፣ ዮዲት መኮንን አማካይ ከአዳማ ፣ ማህሌት ሽፈራው ግብ ጠባቂ ከአርባምንጭ እና አበባ አጀቦ ግብ ጠባቂ ከስፖርት አካዳሚ ክለቡን የተቀላቀሉት ተጫዋቾች ናቸው።

ክለቡ ከአዳዲሶቹ በተጨማሪ የቤተልሄም መንተሎ ፣ መሠረት ማሞ ፣ ሩታ ያደታ ፣ መዲና ጀማል ፣ አይናለም ሽታ ፣ ሰብለ ቶጋ እና አስራት ዐለሙ ለተጨማሪ ዓመት ውላቸው ተራዝሞላቸዋል።