ከፍተኛ ሊግ | ደሴ ከተማ አዲስ አሰልጣኝ ቀጥሯል

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ተወዳዳሪው ደሴ ከተማ ወጣቱን አሰልጣኝ ወደ ኃላፊነት አምጥቷል።

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ላይ የተጠናቀቀውን ዓመት በምድብ ሐ ስር በመደልደል ሲወዳደር የነበረው ደሴ ከተማ ዘንድሮው ተጠናክሮ ለመቅረብ ባሳለፍነው ዓመት በዚሁ ምድብ ገላን ከተማን ወደ ፕሪምየር ሊጉ ለማሳደግ ከጫፍ ደርሶ የነበረው አሰልጣኝ ዳዊት ታደለን አዲሱ የክለቡ አሰልጣኝ በማድረግ ሾሟል።

አሰልጣኝ ዳዊት በአሰልጣኝነት ዘመኑ የአዳማ ከተማን ወጣት ቡድን እንዲሁም ደግሞ ሪፍት ቫሊ ኮሌጅ እና አቃቂ ቃሊቲን በማሰልጠን አሳልፏል። ከአንደኛ ሊጉ ወደ ከፍተኛ ሊጉ ያሳደገውን ገላን ከተማን ዳግም በ2015 ተረክቦ ቡድኑን ጠንካራ ተፎካካሪ ማድረግ ችሎ የነበረው አሰልጣኙ ቀጣዩ መዳረሻው ደሴ ከተማ ስለ መሆኑ ሶከር ኢትዮጵያ ከክለቡ የደረሳት መረጃ ጠቁሟል።