ከፍተኛ ሊግ | ነጌሌ አርሲ የአስራ ሁለት አዳዲስ ተጫዋቾችን ዝውውር አጠናቋል

በኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ላይ ጠንካራ ተፎካካሪ የሆነው ነጌሌ አርሲ አስራ ሁለት አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሟል።

ነገሌ አርሲ ለዘንድሮው የ2016 የከፍተኛ ሊጉ ተሳትፎው በምድብ ለ ስር ከቀናት በፊት የተደለደለ ሲሆን አለብኝ ባለው ክፍተት ላይ በአሰልጣኝ በሽር አብደላ መሪነት ወደ 12 አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል።

ፈራሚዎቹን ስንመለከት ጄብሳ መኢሳ አማካይ ከአውስኮድ ፣ እንዳሻው ታምሬ ተከላካይ ከዳሞት ፣ ምስጋና አንገሳ አጥቂ ከገላን ከተማ ፣ አቤል ፋንታ አማካይ ከሀላባ ፣ ዋንጆ ዋንቆ አማካይ ፣ ከሱሉሉታ ፣ ያሬድ በልጉ ተከላካይ ከእንጂባራ ፣ ሙሉቀን ተስፋዬ አማካይ ከዳሞት ፣ አባተ ዓለሙ ተከላካይ ደቡብ ፖሊስ ፣ ኢብሳ አማን ተከላካይ ከቢሾፍቱ ፣ ሀብትነት ዓለሙ ግብ ጠባቂ ከሻኪሶ ፣ አሸብር ተስፋዬ ግብ ጠባቂ ከየካ እና ተስላች ሳይመን አማካይ ከደሴ ከተማ ክለቡን የተቀላቀሉት አዳዲስ ፈራሚዎች ናቸው። ክለቡ ከአዲሶቹ በተጨማሪ አራት ወጣቶችን ከአካባቢው ስለ መቀላቀሉ ለሶከር ኢትዮጵያ የደረሳት መረጃ አመላክቷል።