አሠልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ስብስባቸውን ይፋ አድርገዋል

አዲሱ የዋልያዎቹ አለቃ ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ሁለት ጨዋታዎች ለተጫዋቾች ጥሪ አቅርበዋል።

ዛሬ እኩለ ቀን አሠልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሠልጣኝ ተደርገው መሾማቸው ይታወቃል። ቡድኑ ከፊቱ ላሉበት ሁለት የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ አዲሱ አሠልጣኝም ለ30 ተጫዋቾች ጥሪ ማቅረባቸውን የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ይፋ አድርጓል።

በአሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ የመጀመርያ ስብስብ ውስጥ የመድኑ የመስመር ተከላካይ ያሬድ ካሳዬ፣ የባህር ዳር ከተማው አማካይ የአብስራ ተስፋዬ፣ የኢትዮጵያ ቡናው ወልደአማኑኤል ጌቱ እና የቅዱስ ጊዮርጊሱ ተገኑ ተሾመ የመጀመርያ የዋና ብሔራዊ ቡድን ጥሪ ሲደርሳቸው ናትናኤል ዘለቀ ከረጅም ዓመታት በኋላ ወደ ብሔራዊ ቡድን የሚመልሰው ጥሪ ደርሶታል። በዲሲፕሊን ጥሰት ከአሜሪካ እንዲመለስ የተደረገው ብርሃኑ በቀለ እና ከብሔራዊ ቡድን ራሱን ማግለሉን ያሳወቀው ጌታነህ ከበደ በስብስቡ ተካተዋል። ጉዳት ላይ የሚገኘው አቡበከር ናስር በአንፃሩ ከኢትዮጵያ ውጪ የሚጫወት ብቸኛው የስብስቡ ተጫዋች ሆኗል።

የተመረጡ ተጫዋቾች 👇

ግብ ጠባቂዎች

ሰዒድ ሀብታሙ (አዳማ ከተማ)፣ አቡበከር ኑራ (ኢትዮጵያ መድን)፣ ቢንያም ገነቱ (ወላይታ ድቻ)

ተከላካዮች

ሄኖክ አዱኛ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ዓለም ብርሃን ይግዛው (ፋሲል ከነማ)፣ ብርሃኑ በቀለ (ሲዳማ ቡና)፣ ያሬድ ባዬ (ባህር ዳር ከተማ)፣ ምኞት ደበበ (ፋሲል ከነማ)፣ ፈቱዲን ጀማል (ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)፣ ሚሊዮን ሰለሞን (ሀዋሳ ከተማ)፣ ወልደአማኑኤል ጌቱ (ኢትዮጵያ ቡና)፣ ረመዳን የሱፍ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ያሬድ ካሳዬ (ኢትዮጵያ መድን)

አማካዮች

ጋቶች ፓኖም (ፋሲል ከነማ)፣ ናትናኤል ዘለቀ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ ሽመልስ በቀለ (መቻል)፣ ሱራፌል ዳኛቸው (ፋሲል ከነማ)፣ ወገኔ ገዛኸኝ (ኢትዮጵያ መድን)፣ የአብስራ ተስፋዬ (ባህር ዳር ከተማ)፣ አለልኝ አዘነ (ባህር ዳር ከተማ)፣ ከነአን ማርክነህ (መቻል)

አጥቂዎች

ጌታነህ ከበደ (ፋሲል ከነማ)፣ ሀብታሙ ታደሰ (ባህር ዳር ከተማ)፣ አቤል ያለው (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፣ አቡበከር ናስር (ማሜሎዲ ሰንዳውንስ/ደቡብ አፍሪካ)፣ አማኑኤል ገ/ሚካኤል (ፋሲል ከነማ)፣ ፍፁም ጥላሁን (ባህር ዳር ከተማ)፣ ቸርነት ጉግሳ (ባህር ዳር ከተማ)፣ በረከት ደስታ (መቻል)፣ ተገኑ ተሾመ (ቅዱስ ጊዮርጊስ)