ዋልያዎቹ የአቋም መፈተሻ ጨዋታ ሊያደርጉ ነው

ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ዝግጅታቸውን እያደረጉ የሚገኙት ዋልያዎቹ የአቋም መለኪያ ጨዋታ ያደርጋሉ።

በአሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ የሚመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከፊታችን ላለበት የዓለም ዋንጫ ማጣርያ ሁለት ጨዋታዎች ዝግጅቱን ማድረግ ከጀመረ አራተኛ ቀኑን እስቆጥሯል። ከአዳማ ወደ አዲስ አበባ በመዞር ዛሬ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሜዳ ረፋድ ላይ ልምምዱን ሰርቶ ያጠናቀቀው ቡድኑ የአቋም መለኪያ ጨዋታን እንደሚያደርግ ታውቋል።

በዚህም መሰረት ብሔራዊ ቡድኑ ነገ ከሱዳኑ አል ሂላል ክለብ ጋር አራት ሰዓት ላይ በባንክ ሜዳ የአቋም መለኪያ ጨዋታውን እንደሚያደርግ ሰምተናል። ዋልያዎቹ 23 ተጫዋቾችን በመያዝ ቅዳሜ ወደ ሞሮኮ የሚያቀኑ ይሆናል።