የኢትዮጵያ ዋንጫ ሁለተኛው ዙር ድልድል ይፋ ሆኗል

የኢትዮጵያ ዋንጫ ከሦስት ዓመት መቋረጥ በኋላ ዘንድ በእግርኳሱ የበላይ አካል የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አወዳዳሪነት ዘንድሮ መጀመሩ ይታወሳል።

የመጀመርያው ዙር የጥሎ ማለፍ ጨዋታ ውድድሮች የከፍተኛ ሊግ ቡድኖችን እርስ በእርስ ያገናኘው ጨዋታ ተከናውኖ አስራ ስድስት ቡድኖች ወደ ሁለተኛው ዙር ማለፋቸው ይታወቃል። ከሁለተኛው ዙር እስከ ፍፃሜው ድረስ የቡድኖች ድልድል በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መሰብሰብያ አደራሽ ተከናውኗል። በዕለቱም የፌዴሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ፣ የፌዴሬሽን የውድድር ባለሙያዎች፣ የሊግ ካምፓኒው ተወካዮች እና የሚዲያ ባለሙያዎች በተገኙበት የዕጣ ማውጣት ሥነ ስርዓቱ ተካሂዷል።

በዚህም መሠረት

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ሀንበሪቾ
ሸገር ከተማ ከ ባህር ዳር ከተማ
ሀድያ ሆሳዕና ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ቤንች ማጂ ቡና ከ ሀዋሳ ከተማ
ከፋ ቡና ከ ሻሸመኔ ከተማ
ወላይታ ድቻ ከ ደሴ ከተማ
ቢሸፍቱ ከተማ ከ ሀላባ ከተማ
አዳማ ከተማ ከ ሲዳማ ቡና
ኢትዮጵያ ቡና ከ ወልድያ ከተማ
ነገሌ አርሲ ከ ስልጤ ወራቤ
ፋሲል ከነማ ከ ነቀምቴ ከተማ
ኦሮምያ ፖሊስ ከ አርባምንጭ ከተማ
መቻል ከ ወልቂጤ ከተማ
ደብረ ብርሀን ከተማ ከ ጋሞ ጨንቻ
ኮልፌ ቀራንዮ ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ
ኢትዮጵያ መድን ከ ድሬደዋ ከተማ

ውድድሩ ከኀዳር 15-17 ባሉት ቀናት ወደፊት በሚገለፅ ቦታ የሚካሄድ ይሆናል።