የቻምፒየንስ ሊግ የሁለተኛ ዙር ማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮጵያውያን ዳኞች ይመራል

አራት ኢትዮጵያዊያን ዳኞች ሞሪታኒያ ላይ የሚደረገውን የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ የሁለተኛ ዙር የማጣሪያ ጨዋታን በዳኝነት ይመሩታል

የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ የሁለተኛው ዙር የማጣሪያ ጨዋታ ከቀናት በኋላ ይጀመራሉ። በምድብ አንድ ስር ተደልድለው የሚገኙት የሞሪታኒያው ክለብ ኖሀዲቡ ከግብፁ ፒራሚድ ጋር ሞሪታንያ በሚገኘው ስታድ ዲላ ካፒታላ ስታዲየም ቅዳሜ ህዳር 22 ምሽት አንድ ሰዓት ላይ ማለትም ከአስራ ሁለት ቀናቶች በኋላ ሲገናኙ ጨዋታው በአራት ኢትዮጵያዊ ዳኞች እንዲመራ ስለ መወሰኑ ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ አመላክቷል።

ጨዋታውን በመሐል ዳኝነት ኢንተርናሽናል ዳኛ በአምላክ ተሰማ ሲመራው ፣ በረዳትነት ደግሞ ኢንተርናሽናል ረዳት ዳኞቹ ትግል ግዛው እና ፋሲካ የኋላሸት ፣ በአራተኛ ዳኝነት ደግሞ ኢንተርናሽናል ዳኛ ቴዎድሮስ ምትኩ ተሰይሟል።