የአሰልጣኞች አስተያየት | ኢትዮጵያ ቡና 1-1 ሀድያ ሆሳዕና

የሳምንቱ የመክፈቻ ጨዋታ በኢትዮጵያ ቡና እና ሀድያ ሆሳዕና መካከል ተደርጎ 1ለ1 በሆነ የአቻ ውጤት ከተቋጨ በኋላ አሰልጣኞች ለሶከር ኢትዮጵያ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

አሰልጣኝ ግርማ ታደሠ – ሀድያ ሆሳዕና

ስለ ጨዋታው …

“ጨዋታው እንደጠበቅነው ነው። ተጋጣሚያችን በጣም ኳስ በደንብ ይዞ የሚጫወት ቡድን ነው ፣ ምናልባት ለዛ የቀረብንበት አቀራረባችን ለእኛ አዋቶናል ካለን ተጫዋቾች አኳያ እንደዚህ አይነት አቀራረብ ቀርበን ይሄንን ውጤት ይዘን መውጣታችን ለእኛ ጥሩ ነው።”

በተከታታይ ጨዋታዎች በመከላከሉ ጥሩ ቢሆኑም በማጥቃቱ ረገድ ስለሚታዩ ክፍተት …

“ከዚህ በፊትም ምናልባት ባለፈው ጨዋታም ላይ እንደዚህ አይነት ችግሮች በደንብ ዛሬ ደግሞ ጎልተው ታይተዋል ፣ ያ ምንድነው ካሉን ተጫዋቾች አቅም አንፃር ባለን ጠንካራ ነገር ነው የምንገባው ወደፊት ያለውን ነገር በጊዜ ሂደት ይስተካከላል ብዬ አስባለሁ አሁን ላለሁ ግን ሌላ አማራጭ የለንም ፣ የመከላከል አቅማችን በጣም የተሻለ እንዲሆን በጣም ጥረት እያደረግን ነው በጣም እየሰራን ነው ያለነው ጎል እንዳይገባብን አቀራረባችን ጥሩ ነው ብዬ አስባለሁ። ዛሬም ያንን ነው የሰራነው ባገኘነው አጋጣሚ ጎል ለማስቆጠር ነው የምንሞክረው አጋጣሚዎች አግኝተናል ፣ ካገኘናቸው አጋጣሚዎች አንዱን ተጠቅመናል ጥሩ ነው ብዬ ነው የማስበው።”

አሰልጣኝ ነፃነት ክብሬ – ኢትዮጵያ ቡና

ስለ ጨዋታው …

“ጨዋታው ጥሩ ነበር ፣ በተለይ ከባለፈው ጨዋታ ከነበረብን ክፍተት አርመን ለመምጣት ሞክረናል መረጋጋቶች ነበሩ ፣ ዛሬ የኳስ ቁጥጥሩ ላይም የተሻልን ነበርን በተወሰነ መልኩ ግን የጎል ዕድሎች መፍጠር ላይ ችግር ነበረብን ፣ ሦስተኛው ሜዳ ስንገባ እርሱን ነገር ነው ቡድናችን ላይ ያየሁት እንጂ በተረፈ ልጆቻችን ያደርጉት የነበረው እንቅስቃሴ ጥሩ ነበር።”

ከሁለት ድሎች በኋላ ቡድኑ በተከታታይ እየተቀዛቀዘ ስለ መገኘቱ…

“በእኔ አልተቀዛቀዘም ፣ የተቀዛቀዘ አይደለም ምክንያቱም ቢያንስ የሚችሉትን ነገር እያደረጉ ነው። ባለፈው ከሻሸመኔ ጋር በነበረው ጨዋታ አንደኛ አጭር ቀኖች ነበሩ በሦስት ቀን ፣ በአራት ቀን ነበር ጨዋታ ያደረግነው ድካሞች ነበሩ ፣ የእነርሱ የእነርሱ ተፅዕኖ ነው ፣ ዛሬ ግን በተወሰነ መልኩ ያንን ነገር ለማስተካከል ሞክረናል ፣ በተጨማሪም ደግሞ የተጎዱብንም ተጫዋቾች አሉ ዛሬ ያልተጠቀምንባቸው የተወሰነ የእነርሱም ተፅዕኖ አለብን የመቀዛቀዝ ነገር የለም። አሁን ቡድኑ ላይ ተጫዋቾቹ ጋር ያለው ከፍተኛ መነሳሳት ነው እንደ አጋጣሚ ሆኖ እግር ኳስ ነውና በውጤት በሁለቱም ጨዋታ ደስተኛ ባንሆንም በእንቅስቃሴ ግን ደስተኛ ነኝ።”

ከረጅም ጊዜ በኋላ ወደ ሜዳ ስለ ተመለሰው አሥራት ቱንጆ

“አስራት ቆይቷን ከጉዳት ከተመለሰ ሜዳ ላይ የመጀመሪያ ጨዋታ ነው ዛሬ ያደረገው ልምምድ ላይ እናየው ነበርና ጤንነቱም በጥሩ ሁኔታ ላይ ነው ያለው ፣ ፊትነሱም ጥሩ ነው ያንን ነገር ነው የጠበቅንበትም እዛ ቦታ ላይ እርሱን ስንጠቀም ተጋጣሚያችን ሜዳውን ዘግቶ እንደሚጫወት ስለምናስብ በኳስ ቁጥጥር የተሻለ እንድንሆን እና ትርፍ ሆነን መሄድ የምንችልባቸውን እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ ነው ፣ እስከ ተጫወተበት ሰዓት ድረስ ጥሩ ነገር ነው ያየውበት ከጨዋታ ጨዋታ እየደገመ ሲሄድ ደግሞ የበለጠ ቡድናችንን ይጠቅማል ብዬ አስባለሁ።”

ቡድኑ እየገጠመው ስላለው ጉዳቶች እና ዛሬም ከባድ ጉዳት ስላስተናገደው መሐመድ ኑርናስር

“ምናልባት ብዙ ኢንፎርሜሽን የለኝም ግን በቃሬዛ እንደሄደ አይቻለሁ። ጉልበቱ አካባቢ ነው አላውቅም ጉዳቱ ምን ያህል ያቆየዋል ግን አሁን ላይ በሙሉ አቅም ነው ጨዋታዎች ማድረግ ያለብን ምናልባት ቀጣይ ጨዋታን ረጅም ጊዜ ቢያንስ የ13 ቀን የዕረፍት ጊዜ ስላለ በእነኚህ ጊዜ ውስጥ የተጎዱብንን ተጫዋቾች አገግመው በድናቸውን ለመጥቀም የተሻለ ነገር አድርገን እንመለሳለን።”