በጨዋታ ዳኞች ላይ የዲሲፒሊን ውሳኔ ተወሰነ

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ዙርያ የብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ የዳኝነት አፈፃፀምን በመገምገም የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል።

የሊጉ ውድድር አስራ አንደኛ ሳምንት ተገባዶ በሚገኝበት በአሁኑ ሰዓት የብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ በየደረጃው የሚገኙ ጨዋታዎች የዳኝነት አፈፃፀማቸውን በመገምገምና በቀጣይ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ የአፈፃፀም አቅጣጫዎችን ከማስቀመጡም በተጨማሪ በልዩ ልዩ የዲስኘሊን ጉድለቶች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን ማሳለፉን የፌዴሬሽኑ መረጃ ያሳያል።

በዚህ መሰረት በአዳማ ከተማ እና በወልቂጤ ከተማ መካከል በተካሄደው የ11ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ኘሪሚየር ሊግ ጨዋታ ላይ ኢንተርናሽናል ረዳት ዳኛ ይበቃል ደሳለኝ በፈፀመው የቴክኒክ ስህተት ምክንያት የብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ ጥፋቱን በጥልቀት ከመረመረ በኋላ የጨዋታ አመራሩ ለ3 ወር ከዳኝነት እንዲታገድ ተወስኗል፡፡

በተጨማሪም ፌደራል ዳኛ ቢንያም ወርቅአገኘሁ እና ፌደራል ዳኛ ብዙወርቅ ኃይሉ በፈፀሙት የዳኝነት አስተዳደራዊ ግድፈት ምክንያት ጉዳዩን በማጣራት የጨዋታ አመራሮችን ሊያስተምር ይችላል በማለት የመጨረሻ የቃል ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል፡፡