አሰልጣኝ አሥራት አባተ እና ድሬዳዋ ከተማ ተለያይተዋል

ብርቱካናማዎቹ ከዋና አሠልጣኛቸው አሥራት አባተ ጋር በስምምነት መለያየታቸውን ይፋ አድርገዋል።


በያዝነው የ2016 ዓ.ም የውድድር ዓመት ካደረጓቸው አሥራ አንድ ጨዋታዎች በሦስቱ አሸንፈው ፣ በሁለቱ አቻ ወጥተው በስድስት ጨዋታዎች በመሸነፍ እና 11 ነጥቦችን በመያዝ 12ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡት ድሬዳዋ ከተማዎች ከዋና አሠልጣኛቸው ጋር በስምምነት መለያየታቸውን የክለቡ የማኅበራዊ ትስስር ገጽ ይፋ አድርጓል።


እንደ ገጹ ዘገባ ከሆነ የቡድኑን የውጤት ማጣት ቀውስ በተመለከተ በዝግ በተደረገው ስብሰባ ዋና አሰልጣኙ ያስገቡት የመልቀቂያ ደብዳቤ ተቀባይነት አግኝቷል።