ኢትዮጵያዊያን ዳኞች ጋቦሮኒ ላይ ነገ ጨዋታ ይመራሉ

ነገ ብሩንዲ እና ቦትስዋና የሚያደርጉት የዓለም ከ17 ዓመት በታች የሴቶች ዋንጫ የማጣሪያ መርሐ-ግብር በአራት ዕንስት ኢትዮጵያዊያን ዳኞች ይመራል።

የ2024 የሴቶች የአለም ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ዋንጫ በስፔን ግዛት ስር በምትገኘዋ ዶሚኒካን ሪፐብሊክ አዘጋጅነት ይከናወናል። በዚህ ውድድር ላይ ለመሳተፍ በአፍሪካ የሚገኙ ሀገራት ከትላንት ጀምሮ የማጣሪያ መርሀግብራቸውን ማድረግ የጀመሩ ሲሆን በነገው ዕለት ማክሰኞ ከቀትር በኋላ 10፡00 ብሩንዲ ሜዳዋ ላይ ማድረግ የነበረባትን ጨዋታ በተጋጣሚያዋ ሀገር ቦስትዋና ጋቦሮኒ ስታዲየም ላይ ስታከናውን አራት ኢትዮጵያዊያን ኢንተርናሽናል ዳኞች ይህንን ጨዋታ እንዲመሩት ስለመመረጣቸው ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ አመላክቷል።

ጨዋታውን በመሐል ዳኝነት መዳብ ወንድሙ ስትመራው ረዳት በመሆን ደግሞ ወይንሸት አበራ እና ብርቱካን ማሞ አራተኛ ዳኛ በመሆን ደግሞ ፀሐይነሽ አበበ በመሆን ተመድበዋል።