የቀድሞ የመቻል ተጫዋች ወደ ዌልስ አቅንቷል

በመቻል የስድስት ወራት ቆይታ የነበረው የመስመር
ተጫዋች የዌልሱን ክለብ ተቀላቅሏል።

ከዓመታት በፊት በዌልስ ሁለተኛ የሊግ እርከን ከሚሳተፈው ባክሊይ ወደ መቻል አቅንቶ ከቡድኑ ጋር የወራት ቆይታ የነበረው አሚን አሐመድ ወደ ቀድሞ ክለቡ ተመልሷል። ባክሊይ የተባለ ክለብ ለቆ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ከመቻል ጋር የስድስት ወራት ቆይታ ካደረገ በኋላ ከክለቡ ጋር በውዝግብ የተለያየው ይህ ተጫዋች ወደ ኢትዮጵያው ክለብ ከመምጣቱ በፊት በኢንግሊዝ ታችኛው ዲቪዝዮን በሚሳተፉት ስካርቦራ፣ ማውስሆልና ማክስፊልድ እንዲሁም አቤሪስትዊትና ባክሊይ በተባሉ የዌልስ ክለባች ቆይታ ነበረው።

ቀደም ብሎ ሌላው ትውልደ ኢትዮጵያዊ ልዑል ወርቅነህ ያስፈረመው ይህ ክለብ በዌልስ ሁለተኛው የሊግ እርከን በሀያ አምስት ነጥቦች አስረኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።