ሎዛ አበራ የአሜሪካውን ክለብ በይፋ ተቀላቀለች

የአሜሪካው ክለብ ማራውደርስ ኢትዮጵያዊቷን አጥቂ ወደ ስብስቡ መቀላቀሉን ይፋ አድርጓል።


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አጥቂ የሆነችው ሎዛ አበራ ከወራት በፊት አሜሪካ በሚገኘው ኤጀንት መዝሙረዳዊት መኩሪያ አመቻችነት ወደ ስፍራው በማቅናት የሙከራ ጊዜያዋን ያሳለፈች ሲሆን ተጫዋቿን ያለፉትን ወራት ያሳለፈችው ሙከራ አመርቂ ሆኖ በመገኘቱ በአሜሪካ “USWL” ሊግ የሚሳተፈው ማራውደርስ እግርኳስ ክለብን የሙከራ ጊዜዋን በስኬት በማጠናቀቋ ወደ ስብስቡ በይፋ መቀላቀሉን ክለቡ ይፋ አድርጓል።


እግር ኳስን ከሀዋሳ ከተማ ከጀመረች በኋላ በመቀጠል በደደቢት ፣ በአዳማ እና ከሀገር ውጪ በሆላንድ ክለቦች የሙከራ እና በማልታው ቢርኪርካራ ደግሞ የተሳካ ቆይታን በማድረግ በእግር ኳስ ህይወቷ የከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነት እና የምርጥ ተጫዋችነት ክብርን በተደጋጋሚ ያገኘቸው አጥቂዋ በሀገር ውጪ የእግር ኳስ ህይወቷ የአሜሪካው ክለብ ሁለተኛው ሆኗል።