ሴካፋ የተለያዩ ውድድሮች ጊዜ እና ቦታ ይፋ አድርጓል

የምስራቅ አፍሪካ እግርኳስ የበላይ አካል የሆነው ሴካፋ በስሩ የሚከናወኑ ስድስት ውድድሮች የማከናወኛ ጊዜ እና ቦታ አስታውቋል።

ሴካፋ በኬንያ ሞምባሳ ባካሄደው ጠቅላላ ጉባዔ በዚህ ዓመት የተለያዩ ውድድሮች እንዲያዘጋጁ የመረጣቸው ሀገራት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። በዚህ መሰረት ኢትዮጵያ የካፍ የሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ የማጣሪያ ውድድርና እና ከ20 አዖዓመት በታች የሴቶች ሻምፒዮና እንድታዘጋጅ መመረጧ ተገልጾ የነበር ሲሆን ከዛ በተጨማሪም ዩጋንዳ የአፍሪካ ዋንጫ ከ17 ዓመት በታች ዋንጫ ማጣርያ ፣ ታንዛኒያ የአፍሪካ ከ20 ዓመት በታች ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታዎችን ፣ ዛንዚባር ደግሞ የ2024 የሴካፋ ዋንጫን የማስተናገድ ዕድል ማግኘታቸው የተረጋገጠ ሲሆን ወድድሮቹ የሚደረጉበትን ቀን ደግሞ ሴካፋ ከደቂቃዎች በፊት ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሰረት ፦

ዛንዚባር የምታዘጋጀው የሴካፋ ዋንጫ ከቅዳሜ ሰኔ 22/2016 እስከ እሁድ ሐምሌ 7/2016

ኢትዮጵያ የምታዘጋጀው የሴቶች ቻምፒዮንስ ሊግ ማጣሪያ ከቅዳሜ ነሐሴ 11/2016 እስከ እሁድ ነሐሴ 26/2016

ታንዛኒያ የምታዘጋጀው ከ20 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከቅዳሜ መስከረም 25/2017 እስከ ቅዳሜ ጥቅምት 9/2017

ዛንዚባር የምታዘጋጀው የአፍሪካ የትምህርት ቤቶች ውድድር ማጣሪያ ከረቡዕ ሕዳር 25 – ሕዳር 28/2017

ኢትዮጵያ የምታዘጋጀው የሴካፋ ከ20 ዓመት በታች ሻምፒዮና በሕዳር ወር

ዩጋንዳ የምታዘጋጀው የአፍሪካ ዋንጫ ከ17 ዓመት በታች ማጣሪያ ከቅዳም ታኅሣሥ 5 – 10/2017 የሚደረጉ ይሆናል።