ከፍተኛ ሊግ | ስልጤ ወራቤ የዕለቱ ብቸኛ ባለድል ሆኗል

የኢትዮጵያ ወንዶች ከፍተኛ ሊግ የ15ኛ ሳምንት በምድብ ሀ ሦስት ጨዋታዎች ተደርገው ሁለቱ በአቻ ውጤት ሲጠናቀቁ ስልጤ ወራቤ ብቻውን ሦስት ነጥብ ያሳካ ክለብ ሆኗል።

ረፋድ 3:00 ሲል የጀመረው መርሃግብር ይርጋጨፌ ቡናን ከስልጤ ወራቤ አገናኝቶ ስልጤ ወራቤ በሁለተኛ አጋማሽ ባስቆጠሩት ግብ አሸናፊ ሆኗል።

ቀዝቃዛው ጨዋታ በስልጤ አሸናፊነት ሲጠናቀቅ ሁለቱም ቡድኖች ከመጀመሪያው አጋማሽ ጀምረው እምብዛም የግብ ሙከራ ያልታየበት ጥሩ የማይባል እንቅስቃሴ አድርገዋል። ሆኖም ግን ስልጤ ወራቤ ከተጋጣሚው የበለጠ የኳስ ቁጥጥር እና የግብ ሙከራ ያደረግ ቡድን ነበር።ይርጋጨፌ ቡና በአንፃሩ በመልሶ ማጥቃት አንዳንድ የግብ ማግባት እድል ለመፍጠር ጥረት ቢያደርግም የስልጤ ወራቤን ግብ መድፈር ከብዷቸዋል።

በ15ኛው ደቂቃ ለስልጤ ወራቤ ኪዳነማርያም ተስፋዬ ግብ ቢያስቆጥርም የእለቱ ዳኛ ከረዳት ዳኛ ጋር በመናበብ የግብ መረብ በመበጠሱ ምክንያት ኳሱ በጀርባ በኩል እንደገባ አሳውቀው ግቡ ተሽሮባቸዋል።በዚህም ግቡ ይገባኛል ክርክር ጨዋታ ለ5 ደቂቃ ለመቋረጥ ተገዷል።የመጀመሪያ አጋማሽ ሊጠናቀቅ 6ደቂቃዎች ሲቀሩት በ39ኛው ደቂቃ በስልጤው ፎዐድ መሐመድ ላይ በተሰራው ጥፋት ፍፁም ቅጣት ምት ለስልጤዎች ተሰጥቷቸዋል።ሆኖም ግን ጌትነት ታፈሰ አምክኖታል።በዚህም የመጀመሪያ አጋማሽ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።

ከመልበሻ ክፍል መልስ ስልጤዎች ከተጋጣሚያቸው የጨዋታ ብልጫ በመወሰድ በኳስ ቁጥጥር በልጠው ተገኝተዋል። ሁለቱም ቡድኖች ጨዋታው ግን ከመጀመሪያው አጋማሽ ይልቅ ሳቢ መሆን የቻለበትን ሁለተኛ አጋማሽ አሳልፈዋል።በ64ኛው ደቂቃ የስልጤው የፊት መስመር ተጫዋች ስዩም ደስታ በአንድ ለአንድ ንክኪ የተገኘውን ኳስ ከመረብ ጋር አገናኝቶ ስልጤ ወራቤ መምራት ችሏል።

ጨዋታው ወደአንድ ጎን ቢያጋድልም ይርጋጨፌ ቡናዎች የአቻነት ግብ ፍለጋ በመነቃቃት የግብ ሙከራ ሲያደርጉ ተስተውለዋል።ሆኖም ግን ጠንካራውን የስልጤ ወራቤን ተከላካይ መስመር አልፈው ግብ ማስቆጠር ተስኗቸዋል።ስልጤ ወራቤም በአንፃሩ ነጥባተውን ለማስጠበቅ ወደኋላ በመመለስ ሲጫወቱ ተስተውለዋል።በዚህም ሌላ ጨማሪ ግብ ሳይቆጠር ጨዋታው 1ለ0 በሆነ ውጤት በስልጤ ወራቤ አሸናፊነት ተጠናቋል።

ቀን 8:00 የተደረገው መርሃግብር ቤንችማጂ ቡናን ከሞጆ ከተማ ያገናኝ ሲሆን ከእረፍት በፊት እና ከእረፍት መልስ በተቆጠሩ ግቦች ነጥብ መጋራት ችለዋል።

በመጀመሪያ አጋማሽ የጨዋታ ብልጫ የወሰዱት ቤንችማጂ ቡናዎች በኳስ ቁጥጥርና ግብ በማስቆጠር ቀዳሚ ነበሩ።በተደጋጋሚ የግብ ሙከራ ካደረጉ በኋላ በ29ኛው ደቂቃ የጥረታቸው ውጤት የሆነችዋን ግብ ሀሰን ሁሴን በእራሱ ጥረት ኳስን ይዞ በመግባት ከመረብ ጋር አገናችቷ ጨዋታውን መመራት እንድችሉ ሆኗል።

ሞጆ ከተማ በአንፃሩ በመጀመሪያ አጋማሽ ደካማ የኳስ ቁጥጥር አስመልክተዋል።አልፈው አልፈው የሚያገኙትን ለግብ የተቃረበ ኳስ ሳይጠቀሙ ቀርተዋል።የአቻነት ግብ ለማስቆጠር ጫና ፈጥረው ቢጫወቱም ግብ ሳያስቆጥሩ በይርጋጨፌ ቡና መሪነት ወደመልበሻ ክፍል አምርተዋል።

ሞጆ ከተማ ከመልበሻ ክፍል መልስ የተጫዋች ቅያሪ በማድረግ የጨዋታ ብልጫ መውሰድ ችለዋል።በዚህም ከእረፍት በተመለሱ በ8ኛው ደቂቃ አቤኔዘር ታደሠ በንክኪ የተገኘቸውን ኳስ ከመረብ ጋር አገናኝቶ አቻ አደርጓቸዋል።አቻ ከሆኑ በኋላ ጨዋታው ተመጣጣኝ የሆነ እንቅስቃሴ አስመልክቷል።

ሁለቱም ቡድኖት የማሸነፊያ ግብ ለማስቆጠር ጥረት አደርገዋል።ሆኖም ግን ቤንችማጂ ቡና በግብ ሙከራ የተሻለ ብልጫ መውሰድ ችለዋል።ቢሆንም ጨዋታው በአቻ ውጤት ሊጠናቀቅ ተገዷል።

የእለቱ የማሳረጊያ መርሃግብር ንብን ከወልዲያ አገናኝቶ ነጥብ ለማጋራት ተገደዋል።

ጥሩ ፉክክር በታየው በዚህ ጨዋታ ሁለቱም ቡድኖች በመጀመሪያ አጋማሽ ብቻ በርከት ያለ የግብ ማግባት ሙከራ አድርገዋል።እንዲሁም በጥሩ እንቀስቃሴ ጋር የታጀበውን ጨዋታ ለተመለካች አስመልክተዋል።ቶሎ ቶሎ ወደተቃራኒ ቡድን እየገቡ በሚያደርጉት በግብ ሙከራ ጨዋታው ሳቢ መሆን ችሏል።

ሆኖም ግን በመጀመሪያ አጋማሽ ሁለቱም ቡድኖች ያገኙትን የግብ ማግባት እድል ሳይጠቀሙ ቀርተው ወደመልበሻ ክፍል ያለምንም ግብ ተመልሰዋል።

ከመልበሻ ክፍል መልስ ንቦች በኳስ ቁጥጥር መብለጥ ችለዋል።በዛውም ልክ ያለቁ ኳሶችን አግንተው ሳይጠቀሙ ሲቀሩ ተስተውለዋል።ወልዲያ በአንፃሩ ግብ እስክቆጠርባቸው ወደኋላ አፈግፍገው ተጫውተዋል።

በ53ኛው ደቂቃ ናትናኤል ሰለሞን ለንቦች ኳስን ከመረብ ጋር አገናኝቶ ቀዳሚ አድርጓቸዋል።የመሪነት ግብ ያስቆጠሩት ንቦች በተራቸው ነጥቡን ለማስጠበቅ ወደኋላ ብለው ተጫውተዋል።አለፈው አልፈውም የግብ ሙከራ አደርገዋል።ወልዲያ በአንፃሩ ግብ ለማስቆጠር በተደጋጋሚ ሙከራ ሲያደርግ ለመመለከት ተችሏል።

በንብ መሪነት መደበኛው የጨዋታ ክፍለጊዜ ተጠናቋል።ሆኖም ተጨማሪ በታየው ውስጥ ወልዲያዎች የንብ ተከላካዮች በሰሩት ጥፋት ፍፁም ቅጣት ምት አግንተዋል።90+3 ላይ ቢኒኑላንቃሞ ፍፁም ቅጣት ምቱን ከመረብ ጋር አገናኝቶ ነጥብ እንዲጋሩ ሆኗል።