የጣና ሞገዶቹ የዚህ ሳምንት ጨዋታ ተራዝሟል

አማካይ ተጫዋቻቸውን በሞት ያጡት ባህር ዳር ከተማዎች ቅዳሜ ከወልቂጤ ጋር ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ ለሌላ ጊዜ ተላልፏል።


በትናንትናው ዕለት ሕይወቱ ያለፈውን አለልኝ አዘነ በክረምቱ የዝውውር መስኮት ከበርካታ ክለቦች ጋር ታግለው ለሦስተኛ የውድድር ዘመን በክለባቸው ማቆየት የቻሉት የባህር ዳር ከተማዎች የቡድን ስብስብ ወደ ተጫዋቹ የትውልድ ቦታ አርባምንጭ በሀዘኑ ላይ ለመገኘት እና ወዳጆቹን ለማጽናናት በመሄዳቸው ቅዳሜ ከሠራተኞቹ ጋር ሊያደርጉት የነበረውን ጨዋታው እንዲራዘምላቸው መጠየቃቸው ታውቋል።


ሆኖም የሊግ አክስዮን ማኅበሩ የባህር ዳር ከተማን ጥያቄ በመቀበል ጨዋታውን ለሌላ ጊዜ ማስተላለፉን ሱፐር ስፖርት ይፋ ያደረገ ሲሆን በቀጣይ መቼ ይደረጋል ለሚለው ጥያቄ ነገ መልስ እንደሚሰጥበት ይጠበቃል።