የዐፄዎቹ የመስመር አጥቂ በጉዳት ለወራት ከሜዳ ይርቃል

ትናንት ፋሲል ከነማ ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረጉት ጨዋታ ከበድ ያለ ህመም ያጋጠመው የመስመር አጥቂው ለወራት ከሜዳ የሚርቅ ይሆናል።

በአስራ ዘጠነኛው ሳምንት ትናት ምሽት በተካሄደው የፋሲል ከነማ እና በኢትዮጵያ ቡና ጨዋታ በአንድ አቻ ውጤት መጠናቀቁ ይታወሳል። በጨዋታው የመጀመርያ አጋማሽ ወቅትም የፋሲል ከነማው የመስመር አጥቂ አማኑኤል ገብረሚካኤል በደረሰበት ከባድ ጉዳት ለተሻለ ህክምና ወደ ሆስፒታል ማምራቱ ይታወቃል።

ሶከር ኢትዮጵያ አሁን ባደረገችው ማጣራት ጉዳቱ ከበድ ያለ እንደሆነ እና የእግራ እግሩ ሁለት አጥንቶቹ ስብራት እንዳጋጠመው ሰምተናል። ይህን ተከትሎ ከህመሙ አገግሞ ወደ ሜዳ ለመመለስ ወራቶች እንደሚያስፈልጉት አውቀናል።