ቅዱስ ጊዮርጊስ አሰልጣኞቹን አገደ

በትላንትናው ዕለት በሀዋሳ ከተማ ሽንፈት ያስተናገዱት ፈረሰኞቹ ሁለት አሰልጣኞችን ሲያግዱ በምትካቸውም አሰልጣኝ ሾመዋል።


በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሀዋሳ ቆይታቸው በትላንትናው ዕለት ከኃይቆቹ ጋር አድርገው የ2ለ1 ሽንፈትን ያስተናገዱት ፈረሰኞቹ የአሰልጣኝ ቡድን አባላቱን ሲያግዱ በምትካቸውም አሰልጣኞችን ሾመዋል። የክለቡ ቦርድ ካደረገው ስብስባ በኋላ ዋና አሰልጣኙ ዘሪሁን ሸንገታ እና የግብ ጠባቂ አሰልጣኙ ውብሸት ደሣለኝን ሲያግድ በምትኩም ረዳት የነበሩትን ደረጀ ተስፋዬ በዋና አሰልጣኝነት ከ20 ዓመት በታች ቡድኑ አሰልጣኝ በመሆን ሲሰሩ የነበሩት ሳምሶን ሙሉጌታን በረዳት አሰልጣኝነት መሾሙን ይፋ አድርጓል።

የፊታችን ዓርብ ቅዱስ ጊዮርጊሶች ኢትዮጵያ መድንን በአዲስ ተሿሚ አሰልጣኞች እየተመሩ የ24ኛ ሳምንት የሊግ ጨዋታቸውን ያከናውናሉ።