ዋልያዎቹ ከስብስባቸው አንድ ተጫዋች ቀንሰዋል

ነገ ወደ ጊኒ ቢሳው የሚያቀናው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከስብስቡ መካከል አንድ ተጫዋች መቀነሱ ታውቋል።

ከፊታቸው ላለባቸው ሁለት ለዓለም ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታዎች ከቀናት በፊት ዝግጅታቸውን የጀመሩት ዋልያዎቹ ነገ ወደ ስፍራው ከማቅናታቸው በፊት አንድ ተጫዋች እንደሚቀንሱ አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ ትናንት በጋዜጣዊ መግለጫ በተናገሩት መሠረት ከብሔራዊ ቡድኑ ከስብስቡ ውጭ የሆነው ተጫዋች ታውቋል።

ከቡድኑ ጋር አብሮ የማይጓዘው ተጫዋች የባህር ዳር ከተማ የፊት መስመር አጥቂ ሀብታሙ ታደሰ መሆኑም ሲታወቅ የቀሩት 23 ተጫዋቾችን በመያዝ ቡድኑ ነገ ማለዳ ወደ ጊኒ ቢሳው የሚጓዙ ይሆናል።